አዝ፦ ቸር ነውና ምህረቱ የለው ወደር ክብር ይሁንለት በሰማይ በምድር እልል በሉ ዘምሩለት በበገና አምልኮ ለእግዚአብሔር ይገባዋልና ይገባዋል (8x) ሰማይና ምድርን በቃሉ ያጸና ሁሉን የፈጠረ ኃያል ባለዝና በእውነት እንደ ቃሉ ፍፁም የታመነ አልፋና ኦሜጋ ኤልሻዳይ የሆነ ዘለዓለማዊ አምላክ ሁሉ ይቻለዋል አምልኮና ስግደት ክብር ይገባዋል ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (4x) አዝ፦ ቸር ነውና ምህረቱ የለው ወደር ክብር ይሁንለት በሰማይ በምድር እልል በሉ ዘምሩለት በበገና አምልኮ ለእግዚአብሔር ይገባዋልና ይገባዋል (8x) የሞት አዋጅ ሽሮ ሕይወትን የሚሰጥ መራራውን ሃዘን በሳቅ የሚለውጥ አጥፊውን አጥፍቶ ምስኪኑን ያከብራል ሃሳቡ እንደዋዛ መቼ ይከለከላል ማደሪያው ይባረክ ክብር ይሁንለት የፍጥረታት ጌታ የሕያዋን አባት ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (4x)