Song Lyrics

አባት አግኝቻለሁ

Tefera Negash
Alimelesim
ጠላቴ ያሻውን ቢያወራ አልሰማም እንኳንስ ልፈራ አምላኬ ጥላ ስር አድራለሁ አስተማማኝ ጋሻ አግኝቻለሁ ዲያቢሎስ ቢፎክር ቢያወራ አልሰማም እንኳንስ ልፈራ አምላኬ ጥላ ስር አድራለሁ የሚያኮራ አባት አግኝቻለሁ አዝ፦ አግኝቻለሁ አባት አግኝቻለሁ (4x) ደሙ በጉ በኔ ላይ ስላለ ጥፋት መቼም አያገኘኝ እንደ ዐይኑ ብሌን ይጠብቀኛል እግዚአብሔር መቼም አይተወኝ ያ የጨለማ ዘመን አለፈ አበቃ ብርሃን በራ አሻገረኝ በበረታች ክንዱ ነፃ ወጣሁ በአምላክ ስራ ፈርዖን ከኋላ ቀይ ባሕር ከፊቴ ከብቦኝ ቢደነፋ ቢፎክር ጠላቴ እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላቶቼ ሁሉ በሰባት መንገድ ይበታተናሉ ኃያሉ ሲነሳ የከበቡኝ ሁሉ በሰባት መንገድ ይበታተናሉ ምድሩን ማዕበሉን አልፈራ እግዚአብሔር በኃይሉ አለ ከእኔ ጋራ በአምላኬ እተማመናለሁ ጠላቴ ይሰጥማል እኔ እሻገራለሁ አዝ፦ አግኝቻለሁ አባት አግኝቻለሁ (4x) ማዕበል ወጀቡ ቢነሳ ተራራው ቢገተር ከፊቴ ሁሉም ትክክል ይሆናል ትዕዛዝ ሲወጣ ከአባቴ መድኃኒቴ ከእኔ ጋር ነው አልፈራም እተማመናለሁ እባቡን እና ዘንዶውን እረጋግጬው አልፋለሁ ሰይጣን ተማምሎ ሊያጠፋኝ ቢነሳ ሊውጠኝ ቢጐመጅ ዙሪያዬን ቢያገሳ ልቤ አይደነግጥም በከንቱ ፉከራ እግዚአብሔር ጋሻዬ አለ ከእኔ ጋራ ልቤ አይደነግጥም በከንቱ ፉከራ እግዚአብሔር አባቴ አለ ከእኔ ጋራ ከእኔ ጋራ አለ ከእኔ ጋራ ከእኔ ጋራ አምላክ ከእኔ ጋራ ከእኔ ጋራ አለ ከእኔ ጋራ ከእኔ ጋራ ጌታ ከኔ ጋራ ፈርዖን ከኋላ ቀይ ባሕር ከፊቴ ከብቦኝ ቢደነፋ ቢፎክር ጠላቴ እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላቶቼ ሁሉ በሰባት መንገድ ይበታተናሉ ኃያሉ ሲነሳ የከበቡኝ ሁሉ በሰባት መንገድ ይበታተናሉ ወጀቡን ማዕበሉን አልፈራ እግዚአብሔር በኃይሉ አለ ከእኔ ጋራ በአምላኬ እተማመናለሁ ጠላቴ ይሰጥማል እኔ እሻገራለሁ አዝ፦ አግኝቻለሁ አባት አግኝቻለሁ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection