Song Lyrics

ፀጋህ ያግዘኝ

Tefera Negash
Alimelesim
መንፈስህ ይምራኝ እንጂ ምን አቅም አለኝ እኔ በአንተው ነው ሰው መሆኔ (2x) ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (2x) የዘለዓለም እቅድህ በእኔ ያለህን አላማ ፈጽሜ ደስ እንዳሰኝህ እርዳኝ ከሃሳብህ ልስማማ በሚሰማ በሚታየው እንዳልወሰድ ከቤትህ ምራኝ እጆቼን ያዝና ሁልጊዜ ልኑር በፊትህ (2x) እርዳኝ እንዳላሳዝንህ እርዳኝ (3x) እርዳኝ በቤትህ እንድኖር እርዳኝ አዝ፦ ፀጋህ ያግዘኝ እንጂ መንፈስህ ይምራኝ እንጂ ምን አቅም አለኝ እኔ በአንተ ነው ሰው መሆኔ (2x) ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (ጌታዬ) አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (2x) እምነት እንደጐደለው ሰው መጠራቴ እንዳይቀር ልብህ የፈቃድህን ሚስጥር እንዳውቅ ጥበብ ማስተዋልን ስጠኝ ስንፍናዬ ከኔ ርቆ እንዲያምር መጨረሻዬ መልካም ፍሬ እንዲገኝብኝ ደግፈኝ ከመነሻዬ (2x) እርዳኝ (እርዳኝ) እንዳላሳዝንህ እርዳኝ (3x) እርዳኝ (እርዳኝ) በቤትህ እንድኖር እርዳኝ አዝ፦ ፀጋህ ያግዘኝ እንጂ መንፈስህ ይምራኝ እንጂ ምን አቅም አለኝ እኔ በአንተ ነው ሰው መሆኔ (2x) ጌታዬ ጌታዬ ጌታዬ (ጌታዬ) አንተ ነህ ለእኔ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection