እወድሃለሁ ጌታ አድነኸኛል አመልክሃለሁ ኢየሱስ ቤዛ ሆነኸኛል አመሰግናለሁ ጌታ ታድገኸኛል አከብርሃለሁ ኢየሱስ ልጅ አድርገኸኛል ላመስግንህ ጠዋትና ማታ ከዚህ በላይ ይገባሃል ጌታ ላመስግንህ ጠዋትና ማታ ይሄ ብቻ አይበቃህም ጌታ ከሞት መንደር በምህረትህ በቸርነትህ አውጥተህ ጨለማውን አስወግደህ ለዚህ ክብር ያበቃኸኝ ሳትሰለች እያባበልክ ከኃጢአት በደሌን ታግሰህ ሰው አረግከኝ አተረፍከኝ ነፍሴን ከጥፋት መልሰህ አዝ፦ ባለውለታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ጌታዬ ዋሴ ጠበቃዬ (2x) ያለ እረኛ ስቅበዘበዝ በዓለም ወጥመድ ተይዤ ፈጣሪዬን ስበድል ሳሳዝን በክፉ ደንዝዤ እራራህልኝ ደረስክልኝ ጸያፍ ታሪኬን ቀየርከው ልጅ ተባልኩኝ ክብር አገኘሁ ስሜን በደም ቀለም ጻፍከው አዝ፦ ባለውለታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ጌታዬ ዋሴ ጠበቃዬ (2x)