Song Lyrics

ምሥጋና

Tefera Negash
Alimelesim
አዝ፦ ስራዬን ሰርተህልኛል እዳዬን ከፍለህልኛል መንገዴ ተቃንቶልኛል አንተን ማየት ሆኖልኛል በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (4x) አንተ የደስታዬ ምንጭ ውዴ የሰላሜ ንጉሥ ከትቢያ ላይ ያነሳኸኝ ክበር ተመስገን ኢየሱስ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ አይቻለሁ ማዳንህን ሳልታክት አወራዋለሁ አምላኬ ሕያው ስራህን በተከበበ ከተማ ምህረትህ በዝቶልኝ በድል መንገድ እየመራህ ከጠላቴ አስጥለኀኝ የሞተውን ማንነቴን ሕይወት ዘርተህበታል ከብረህልኛል በቤቴ በረከትህ በርክቷል (2x) አዝ፦ ስራዬን ሰርተህልኛል እዳዬን ከፍለህልኛል መንገዴ ተቃንቶልኛል አንተን ማየት ሆኖልኛል በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (4x) የዓለም እንከን የሞላበት ውል አልባ ሆኖ መንገዴ አንተን እንዳላይ ከልሎኝ አጉል ወግና ልማዴ ምንም በጐነት ሳይኖረኝ እንዲያው ምህረት አግኝቼ የደምህ ፍሬ ሆኛለሁ ከኀጢአት ባሕር ወጥቼ ምሥጋናዬን ልሰዋልህ ክበርልኝ ዘለዓለም በዘመኔ ሁሉ ለእኔ እንዳንተ መልካም የለም እፎይ ብያለሁ አርፌ ሆነኸኛል ሰላሜ ተባረክልኝ ልበልህ ደግሜ ደጋግሜ (2x) አዝ፦ በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (4x) የሞተውን ማንነት ሕይወትን ዘርተህበት ጽድቅህን ሰጥተኸኝ ለእኔ ነፃ አረግከኝ ከኩነኔ አዝ፦ በዘለዓለም ፍቅርህ ወድደኸኛልና ምሥጋና አይጠፋም ከአፌ ምሥጋና (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection