Song Lyrics

ገለል ይላል

Tefera Negash
Alimelesim
እኔ ግን ሁሉን ለሚችለው ለርሱ ተለይቻለሁ በተቀደሰው ተራራዬ ንጉሤን ሾሜዋለሁ (2x) አመልከዋለሁ በቤቴ አከብረዋለሁ አነግሰዋለሁ በልቤ እቀድሰዋለሁ (2x) ከተነገረለት ከተባለው በላይ ትልቅ ነው አምላኬ በምድር በሰማይ እሰግድለታለሁ ይገባዋል እሱ ከፍ አደርገዋለሁ በቤተ መቅደሱ ኤልሻዳዩን አምላክ ሳመልከው ከልቤ (2x) ስሙን ሳወድሰው በፍፁም ሃሳቤ (2x) ምን ይሳነዋል ጌታ ታምራት ይሆናል (2x) የሚገዳደረኝም ጥሎኝ ገለል ይላል አዝ፦ ገለል ይላል (3x) ከፊቴ ገለል ይላል (2x) ቢመከር ቢዶለት ወጥመድ ቢዘረጋ የጠላት ሠራዊት ሺህ ሆኖ ቢንጋጋ እውነት እንደ ጋሻ ዙሪያዬን ከብቦኝ ምልክት አለብኝ በየት ሊያገኘኝ በነፍሥም እንኳን ቢሆንም እወራረዳለሁ (2x) ከሚነድም እሳት ያድናል አምናለሁ (2x) የቃልኪዳን ልጅ ነኝ ይሄው ነው ትምክህቴ ጌታ ነው ትምክህቴ ጭንገፋና እርግማን አይገቡም በቤቴ (2x) የጌታን ሥም ስጠራ ችግር ቢሆን መከራ ኢየሱስን ስጠራ ሸለቆ ቢሆን ተራራ የስልጣኑን ጉልበት መቼ ይቋቋማል አዝ፦ ገለል ይላል ከፊቴ ገለል ይላል (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection