ልዑል ነህ ተብሎ በፈርዖን ቤት ስፍራው እንዳልሆነ ሲገባው እውነት ሁሉን ክብር ትቶ መረጠ መከራ ተስማማ ጨክኖ ከፈጣሪው ጋራ (2x) በዐይን ከሚታየው ይልቅ የማይታየውን አምኖ የዘለዓለም መታመኛው መኖሪያው እግዚአብሔር ሆኖ ተሰደደ ሁሉን ትቶ ችግር መከራን ሳይፈራ በእውነት አድርጓልና መንገዱን ከእግዚአብሔር ጋራ (አመነ እግዚአብሔርን አመነ) በትህትና ታዘዘ (ለእውነት ለመታዘዝ ጨከነ) ወደ ምድረ በዳ ተጓዘ (አመነ እግዚአብሔርን አመነ) ትኩር ብሎ አይቶ የሩቁን (ለእውነት ለመታዘዝ ጨከነ) የተጠበቀለት እርስቱን (አመነ እግዚአብሔርን አመነ) በእውነት እግዚአብሔር ይታመናል (4x) ዛሬም ዋጋውን ተምኖ ከልቡ ታዛዥ የሆነ ከመልካም ነገር አይጐድልም ለአምላኩ የታመነ ምንም ፈተናው ቢበዛ የጊዜው ችግር መከራ በአሸናፊነት ይኖራል የሕይወት ፍሬ እያፈራ (በእውነት እግዚአብሔር ይታመናል) ለጥሪው ምላሽ ለሰጠ (እንዳለው እንደ ቃሉ ያደርጋል) በነፍሱ ሳይቀር ለቆረጠ (በእውነት እግዚአብሔር ይታመናል) የድል አክሊል ሽልማት (እንዳለው እንደ ቃሉ ያደርጋል) አይቀርም በጊዜው በወቅቱ (እንዳለው እንደ ቃሉ) በእውነት እግዚአብሔር ይታመናል (4x) በኀጢአት ከሚገኘው ደስታ ይሻላል ታምኖ መኖር በጌታ የፈርዖንን ሹመት ተረድቶ ተሰደደ ሙሴ ክርስቶስን መርጦ ምን ቢበዛ መከራና ስደቱ በሰማይ የድል አክሊል ነው ሽልማቱ