እግዚአብሔር መልካም ነው መልካም ነው በመከራ ቀን መሸሸጊያ ነው አምላካችን መልካም ነው መልካም ነው በመከራ ቀን መሸሸጊያ ነው በመልካም መንገድ የሚመራ ያመኑትን የማያሳፍር ለተጨነቁት ፈጥኖ ደራሽ ታማኝ ነው ቃሉን የሚያከብር ዝናብ ደመና በሌለበት ምድረ በዳውን አለምልሞ በፍፁም በረከት ያኖራል በድንቅ ስራው አስገርሞ አዝ፦ መልካም ነው እግዚአብሔር መልካም ነው (መልካም) (4x) መሸሸጊያ ነው መሸሸጊያ መሸሸጊያ (4x) እያየሁኝ ሲረዳኝ እንዴት ዝም እላለሁኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ብዬ እቀኛለሁ እያየሁኝ ሲረዳኝ እንዴት ዝም እላለሁኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ብዬ እቀኛለሁ አዝ፦ መልካም ነው እግዚአብሔር መልካም ነው (መልካም ነው) (4x) ሁን ያለው ሁሉ የሚሆንለት ሥሙ ገናና የከበረ ሃሳቡ የማይከለከል ያለ የሚኖር የነበረ አዋጅ ገልብጦ የሚያከብር ከእቶን እሳት የሚያድን መልካም እረኛ የት ይገኛል እንደ ክርስቶስ የሚሆን አዝ፦ መልካም ነው እግዚአብሔር መልካም ነው (መልካም ነው) (4x) እያየሁኝ ሲረዳኝ እንዴት ዝም እላለሁኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ብዬ እቀኛለሁ (2x)