Song Lyrics

ዘምበል አለልኝ

Tefera Negash
Alimelesim
እግዚአብሔርን ቆይቼ ደጅ ጠናሁት ሁሉ በእርሱ እንደሚሆን ስላመንኩት እርሱም ጩኸቴን ሰምቶ አዘነልኝ ዘንበል አለልኝ ወደኔ ዘንበል አለልኝ (2x) ከረግረጉ ጭቃ ከጥፋትም ጉድጓድ ከአስፈሪው ጨለማ ከሰይጣንም ወጥመድ አስመለጠን ጌታ በዛ ቸርነቱ ምርኮዬም ተመለሰ አበራልኝ ፊቱ አዝ፦ (ቸር ነው) ከለመንኩት በላይ አብልጦ (ቸር ነው) እጅግ ብዙ አደረገልኝ (ቸር ነው) ተትረፈረፈልኝ ምህረቱ (ቸር ነው) ከአይምሮዬ በላይ ሆነብኝ ጩኸቴን ሰማና አለሁ አለኝ ከሞት አስጣለኝ የማይገባኝን ክብር አገኘሁ ልጁ ተሰኘሁ በእጆቹ መዳፍ ላይ ቀርጾኛል ምን ያስፈራኛል ምህረትና ቸርነቱ ይከተሉኛል እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደሃሳቡም ለተጠሩት እንደሚናገር ቅዱስ ቃሉ ለበጐ ነው ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ቆይቼ ደጅ ጠናሁት ሁሉ በእርሱ እንደሚሆን ስላመንኩት እርሱም ጩኸቴን ሰምቶ አዘነልኝ ዘንበል አለልኝ ወደኔ ዘንበል አለልኝ (2x) አልቀረም በከንቱ ጩኸት ልመናዬ በጊዜው መለሰልኝ ታማኙ ጌታዬ ውድቀቴን የሚሹት አለቀለት ሲሉ ለበጐ አደረገልኝ መከራዬን ሁሉ አዝ፦ (ቸር ነው) ቃልኪዳኑን ከቶ የማይረሳ (ቸር ነው) የወደቁትን የሚያነሳ (ቸር ነው) ለታመኑት የማያሳፍር (ቸር ነው) ከትቢያ አንስቶ የሚያከብር የዘገየ መስሎ ሁሌ ፊት ይገኛል (2x) በሞተው ነገር ላይ ሕይወትን ይዘራል (2x) የጸና ግንብ ነው ለአመኑት የእርሱ ሥም የእግዚአብሔር ሥም ወደርሱ የሮጠ አፍሮ አይመለሥም ከስሮ አይመለስም እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደሃሳቡም ለተጠሩት እንደሚናገር ቅዱስ ቃሉ ለበጐ ነው ነገር ሁሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection