Song Lyrics

ሃገር አለኝ

Tefera Negash
Alimelesim
በጐህ ብርሃን ወደ ሆነላት ከተማ ላልመለስ ከልብ ወስኛለሁ በዓላማ እጓዛለሁ እሄዳለሁ ጠባቡን መንገድ ይዣለሁ በዘመኑ መጨረሻ ከአምላኬ ጋር እኖራለሁ የልጁን መልክ እንድመስል ተወስኖልኛል ከምድር ሕይወቴ ባሻገር ሰማይ ክብር ይጠብቀኛል ጊዜው ሲደርስ የሚገለጥ በእውነት የሚታይ በክርስቶስ የወረስኩት ሃገር አለኝ በሰማይ አዝ፦ ሃገር አለኝ በሰማይ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) እርስት አለኝ በሰማይ እርስት አለኝ (እርስት አለኝ) እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) ከከፍታዬ ላይ በጭራሽ አልወርድም ወደፊት እያየሁ ወደኋላ አልሄድም ኃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ በክርስቶስ ፀጋ በድል እጓዛለሁ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም እገባለሁ (2x) ምንም አስቸጋሪ ቢሆን መውደቅ መነሳቱ ላይደክም ላይዝል ጉልበቴ ጌታ አድርጐኛል ብርቱ ጉዞው በድል ሲጠናቀቅ ህልሜ ግብ ሲመታ ከበጉ ጋር እኖራለሁ ፍፁም በሆነ ደስታ አዝ፦ ሃገር አለኝ በሰማይ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) እርስት አለኝ በሰማይ እርስት አለኝ (እርስት አለኝ) እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ ሃገር አለኝ (ሃገር አለኝ) ሃገር አለኝ በሰማይ ሃገር አለኝ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ ሃገር አለኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection