Song Lyrics

ተመስገን

Tagay Woldemariam
Bizu Zemen Yeteshekemkegn
አዝ፦ተመስገን ጌታዬ ተመስገን ተመስገን አምላኬ ተመስገን (4x) እንደ እናት በጀርባ አዝለህ አሳደግከኝ ክፉም እንዳይነካኝ በእጅግ ሰወርከኝ ውበት ደም ግባቴ ሞገሴ ሆንክልኝ እኔም ዝም አልልም ለአንተ አዜማለሁኝ አዝ፦ተመስገን ጌታዬ ተመስገን ተመስገን አምላኬ ተመስገን (4x) ሁልጊዜ ሳስበው ለኔ ያደረከውን ቃላቶች ያጥሩኛል አንተን ለማመስገን በብዙ ሃጥያቴ ዘወትር ሳስቸግርህ በፊትህ አልጣልከኝም አምላኬ አቆመኝ ምህረትህ አዝ፦ተመስገን ጌታዬ ተመስገን ተመስገን አምላኬ ተመስገን (4x) ብዙ ማይታለፍ ተራራ ሸለቆ አምላኬ አንተ ነህ ያሳለፍከኝ እኮ እኔስ የአንተ ውለታ ከልቤ አይጠፋም ሁሌ አዜመዋለሁ ላፍታ ዝም አልልም አዝ፦ተመስገን ጌታዬ ተመስገን ተመስገን አምላኬ ተመስገን (4x) ለዓለም ለሚመጣው ትውልድ አወራለሁ ያደረክልኝን እመሰክራለሁ ብዙ ዘመናትን ወራት ዓመታትን በእራሴ አይደለም ያለፍኩት በአንተ ነው ተመስገን አዝ፦ተመስገን ጌታዬ ተመስገን ተመስገን አምላኬ ተመስገን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection