Song Lyrics

አዜምለታለሁ

Tagay Woldemariam
Bizu Zemen Yeteshekemkegn
አዝ፦ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደወጣሁ ከጨለማ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደገባኝ የአንተ አላማ አላማህ በእኔ ላይ ፍቅር ሆኖ እንጂ አይገባም ነበር ልትሆነኝ ወዳጅ ይህንን እያሰብኩ ሁሌ አመልክሃለሁ ጠላቴ እየሰማ ዘምርልሃለሁ) (3x) አዝ፦ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደወጣሁ ከጨለማ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደገባኝ የአንተ አላማ የሰላም ሃሳብ ነው የምታስብልኝ ፍጻሜና ተስፋ እንዲሆንልኝ እኔም ከፈቃድህ በፍፁም አልወጣም ከአንተ ተለይቼ መኖር አልመኝም (3x) አዝ፦ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደወጣሁ ከጨለማ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደገባኝ የአንተ አላማ በሃጥያቴ ምክንያት ሞት ተፈርዶብኝ ለሲኦል ለእሳት የታጨሁ ሳለሁኝ አምላኬ ግን ፍቅርህ ለእኔ ስለበዛ ከሞት አመለጥኩኝ ስለሆንከኝ ቤዛ (3x) አዝ፦ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደወጣሁ ከጨለማ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደገባኝ የአንተ አላማ ፍቅርህን በሞትህ ስለገለጽክልኝ የዘለዓለም ሕይወት በነጻ አገኘሁኝ ክብሬን እያየሁ በአንተ ዘንድ ያለውን አዜምልሃለሁ እጅግ ደስ እያለኝ (2x) አዜምልሃለሁ በአንተ ደስ እያለኝ አዝ፦ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደወጣሁ ከጨለማ በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና እኔም ላክብርህ በዜማ እንደገባኝ የአንተ አላማ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection