Song Lyrics

አምላኬን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ

Tagay Woldemariam
Bizu Zemen Yeteshekemkegn
አዝ፦ አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ዘወተር ዘወትር በአፌ ነው (2x) በጠዋት በማታ በቀን በሌሊት ምሥጋናዬ ይድረስ ዘወትር በእርሱ ፊት የአንደበቴን ፍሬ ከቶ አልቆጥብም ብዙ አድርጐልኛል አሃሃ ችዬ ዝም አልልም አዝ፦ አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (2x) የሕይወቴ ጋሻ ተገን ሆኖልኛል ስወጣም ሰገባም እረፍቱ ከቦኛል እርሱን ለማመስገን በገናዬን ላንሳ ያደረገልኝን በፍፁም ሳልረሳ አዝ፦ አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (2x) ስላደረገልኝ እጅግ ብዙ ውለታ አመልከዋለሁኝ ሳልሰለች ለአንድ አፍታ ከዚህ ሌላ ምለው ምሰጠው የለኝም ዘምርለታለሁ እኔስ እስከ ዘለዓለም አዝ፦ አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (2x) አቻምናን ማለፌ ሲደንቀኝ አምናን በምህረትህ አለፍኩኝ ለዘንድሮም ቢሆን አልፈራም ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም (3x) ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም (3x) ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም እጅግ ብዙ ውለታ ለነፍሴ አድርገህላታል ኢየሱሴ (2x) አሳቤን ጭንቀቴን ወስደሃል አምላኬ አሳርፈኸኛል በሕይወቴ ልትኖር መርጠሃል የእኔንም ምሥጋና ወድሃል (2x) የእኔንም ምሥጋና ወደሃል መርጠሃል መርጠሃል የእኔንም አምልኮ መርጠሃል እጅግ ብዙ ውለታ ለነፍሴ አድርገህላታል ኢየሱሴ (6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection