ክብሬን ሁሉ ጥዬ ለአንተ እሰግዳለሁ የሽቶዬን ብልቃጥ በፊትህ አሰብራለሁ አግርህ ስር ወድቄ አገዛልሃለሁ ላከበርከኝ ጌታ ይህም ሲያንስህ ነው (2x) አዝ፦ ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (2x) በምንስ ጀምሬ በምን ልጨርሰው ጌታ ውለታህን በምን ቃል ልግለጸው እንዲያው ዝም ብዬ ክብርን አሰጥሃለሁ በብዙ ምሥጋና ፊትህ እቀርባለሁ (2x) አዝ፦ ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (2x) ኧረ እኔስ ምህረትህ እጅግ በዝቶልኛል ብዙ ኃጢአቴን ይቅር ብለኸኛል በዘመኔ ሁሉ ለአንተ እገዛለሁ በገናዬን ይዤ ፊትህ እዘምራለሁ (2x) አዝ፦ ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (2x) እኔም እንዳከብርህ አንተ መርጠኸኛል በሞገስ ላይ ሞገስ ደርበህልኛል ሁልጊዜ በደስታ አዜምልሃለሁ ራሴን ዝቅ በማድረግ አንተን አክብራለሁ (2x) አዝ፦ ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (2x)