አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው ይቅር ስላለኝ ብዙ በደሌን ቆሜ ለመሄድ በቃሁኝ እኔ በቀን ውሎዬ ምሕረቱ በዝቶ ስሙን እንዳስብ ሆነኝ መከታ አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው ተከብቤያለሁ በእርሱ ቸርነት ጠላቴ እንዳያይ በመግባት መውጣት እጁን በላዬ ያወዛውዛል ዛሬም ለነገ ምሕረቱ በዝቷል አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው ልዘምርለት ስሙን ላክብረው ወዶ ያዳነኝ ጌታ ኢየሱስ ነው ምሕረቱ እኔን ከቦኛልና ለሥሙ ክብር ይሁን ምሥጋና አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው ኢየሱስ ምሕረቱ ለዘለዓለም ናት በእርሱ ሆነልኝ ወደ ዓብ መግባት ከቶ አልታጣም ዘወትር ከፊቱ ከቁጣው ይልቅ በዝቷል ምሕረቱ አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው በፍርሃት ውስጥ በጭንቅ ተይዤ የልቤን አምላክ ፊቱን ፈልጌ ዘወር ብሎ መጣ እኔን አሰበኝ ሥሙ ይባረክ! ፈጥኖ የታደገኝ አዝ፦ ላመስግነው (4x) ምሕረቱ ብዙ ነው ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ነው ይቅርታው