እንደ እርሱ ያለ አላገኘሁም ብወጣ ብወርድ ከቶ አላየሁም የሚደግፍ የሚረዳ የሚያቆም የእኔ ጌታ ማንን ጥሎ እርሱ ያውቃል ለሚጠሩት ፈጥኖ ይደርሳል ጌታ ብቻ ለሁሉ ይበቃል (2x) እርሱን የታመነ በመንገዱ ሁሉ አይወድቅም ዘለዓለም ያቆመዋል ቃሉ በጨለማው ዓለም ብርሃን እየሆነው ይመራዋል ጌታ ቅጥር እያዘለለው ከጠላት ተናጥቀህ ለዚህ ያበቃኸን ኃይልህንም ልከህ እኛን የረዳኸን በመንገዳችን ላይ ቸርነት አድርገሃል ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ክብር ይገባሃል አያስፈልግ ሌላ ሁልጊዜ በቂ ነህ ዘወትር ከለላ ድጋፍ መመኪያ ነህ አንተን የተጠጋህ የተማጸነህ ሰው የጠላትን ሰፈር አተረማመሰው አመልን አዋቂ ገበናን ሸፋኝ ነህ አንተ የናዝሬት ሰው ዘወትር መልካም ነህ ሁሉን እንደ ዓመሉ ችለህ ታኖራለህ አትለወጥ አንተ ዛሬም ነገም ያው ነህ