አዝ፦ ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም ይዘመርልህ ጌታ ጌታ ነህ ማነው እንዳንተ የተከበረ? በኃይሉ ሥልጣን ያልተደፈረ ከጥንት የነበረው ዛሬም ደግሞ ያለው እኛ የምናመልከው ሥሙ እግዚአብሔር ነው አልተለወጠም ዛሬም ሕያው ነው የእኛ ኢየሱስ ብርቱ አምላክ ነው አዝ፦ ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም ምሕረት ዕውነቱ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ ያልተለወጠ ዕውነቱ ከምድር እስከ ሰማይ ያለው ሰላምን ለሕዝቡ ሁሌ የሚናገረው ያየነው ዕውነት እርሱ ታላቅ ነው ተወዳዳሪ ምን መሳይ አለው? አዝ፦ ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም ጌታ እንዳንተ ማን ብርቱ አለ? ሳይሰጋ ከቶ በክብር ያለ በተዘረጋ ክንዱ ሁሉን በሚችለው ተአምራት በመሥራት ስሙን ያስከበረው የአብርሃም አምላክ ዛሬም ሕያው ነው ኃያል ሥም ያለው ጌታ ጌታ ነው አዝ፦ ከአንተ በቀር ኃያል ማንም የለም እግዚአብሔር ብርቱ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ኦሆ! ማንም የለም ስመ ብርቱ ነህ ጌታ ለዘለዓለም