አዝ፦ ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት? ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት ዝም ያሰኘለት? ተራራ ላይ ሆኖ ጠላቴ ሲፎክር የማይወድቅ መስሎት ሕይወቴን ሲያሸብር በሰማይ የሚኖር አምላክ የሆነው ከከፍታ አውርዶ በእግሬ ሥር ጣለው አዝ፦ ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት? ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት ዝም ያሰኘለት? ዘወትር ዕንቅፋትን በፊቴ ላይ ሲያኖር ከበነዋል በቃ ! እያለ ሲፎክር መብረቁን ልኮ ጌታ አወካቸው ዳግም ላይነሱ በጥልቅ ጣላቸው አዝ፦ ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት? ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት ዝም ያሰኘለት? ነበረብኝ ብዙ ሸክም የሆነብኝ ልቤንም አቅልጦት በጣም ያስጨነቀኝ ጌታ ደርሶልኝ እኔን አስጥሎኛል በቅዱሱ ማደሪያው እንዳርፍ እረድቶኛል አዝ፦ ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት? ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት ዝም ያሰኘለት? እንደዚህ እረድቶኝ ከጠላት ድኛለሁ በማያልቅ ፍቅሩ ጸንቼ ቆሜያለሁ ከእንግዲህ በቃ ጌታ ይቀድመኛል ስለሚዋጋልኝ ማክበር ይገባኛል አዝ፦ ማነው እንደ እኔ እግዚአብሔር የተዋጋለት? ከፊቱ ወጥቶ ጠላትን ሁሉ ድል የነሳለት ዝም ያሰኘለት?