Song Lyrics

እንዳንተ ማን ነው

Tadesse Mekuria
Tamagn New Egziabher
አዝ ፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (4x) በጨለማ ብርሃን ነህ በሃዘንም ደስታ ነህ ለታመመው መድሃኒት ነህ ፍፁም ፈውስም በእጅህ አለ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማነኝ ? (4x) ቤቴስ ምንድነው ? የማይገባኝን ክብር በአንተ አገኘሁ ጌታ ተመስገን ! ሁሉ በአንተ ሆኗል ከእኔ የሆነ የለም አንተን የታመነ መች ወድቋል? ዘለዓለም በጥላህ ይኖራል በምትችለው በአንተ መመካት ይሻላል ይጠቅማል መኩራራት ! ተነሣሁ ከአመድ ከትቢያ ረዳኸኝ አንተ ብርቱ ጌታ ! የዜማ ጊዜ ደረሰልኝ ! ስምህን ለማክበር በቃሁኝ ! አዝ ፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (4x) በጨለማ ብርሃን ነህ በሃዘንም ደስታ ነህ ለታመመው መድሃኒት ነህ ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማነኝ ? (4x) ቤቴስ ምንድነው ? ቅጥርን ማዘለል ማበርታት ታውቃለህ ለደካማው ኃይልን ብርታት ትሰጣለህ ማለዳ ማለዳ ኃይልህን በመከራ ጊዜ ማዳንህ የማይዘነጋ ነው ፍቅርህ የየቀኑ ታላቅ ምክርህ አዝ ፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (4x) በጨለማ ብርሃን ነህ በሃዘንም ደስታ ነህ ለታመመው መድሃኒት ነህ ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማነኝ ? (4x) ቤቴስ ምንድነው ? ያደረግኸው ለእኔ እጅጉን ብዙ ነው ጌታ ተመስገን ! የውለታህም ልክ ከምለው በላይ ነው እጅህ የማይደክም ሁልጊዜ ጽኑ መከታ ነህ ለነፍሴ ማረፍ በአንተ ብቻ ነው ዘወትር ስምህን ማክበር ነው አዝ ፣ኧረ እንዳንተ ማነው ? (4x) በጨለማ ብርሃን ነህ በሃዘንም ደስታ ነህ ለታመመው መድሃኒት ነህ ፍፁም ፈውሥም በእጅህ አለ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማነኝ ? (4x) ቤቴስ ምንድነው ?
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection