Song Lyrics

በሥሙ ጉልበት እታመናለሁ

Tadesse Mekuria
Tamagn New Egziabher
አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ! ገና ገና ከጅምሩ እኔን የመረጠኝ የወደደኝ ያከበረኝ ሙሉ መብት የሰጠኝ የከሳሼን ግንባር መቶ ፊቴ የዘረረው የማመልከው እግዚአብሔር ያለ የሚኖረው አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ! ለነአብርሃም ለነይስሐቅ አምላክ የሆናቸው ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጐም ከእሣት ያወጣቸው ለነጳውሎስ በደማስቆ ተገልጦ የታያቸው እርሱ እኮ ነው የእኛ ጌታ ሥልጣን በእጁ ያለው አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ! ኤልያስን የሚሰማ ሲጣራ በቅጽበት ድንቅ አድራጊ ኃያል ጌታ የሚመልስ በእሣት አያሳፍር የበረታው በብርታቱ ታምኖ ያኖረናል እየሠራ ጠላትን አባሮ አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ! እግዚአብሔር ዓብ ለአንድ ልጅ ሙሉ መብት የሰጠው ጌታ ኢየሱስ ለእኛ ደግሞ እንዲሁ አሳለፈው በደዌ አልጋ ለማቀቀው በእሥራት ለኖረው መፍትሔ አለው የኢየሱስ ሥም ከእሥር ገላጋይ ነው አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ! የአምላኬ ሥም የጸና ነው ዛሬም ለዘለዓለም የሚሠራ ኃይሉ ከቶ ጉልበቱ የማይደክም በሰማይም በምድርም ያሻውን ያደርጋል የሚከለክለው የለም በሥልጣን ይሠራል አዝ፦ የእባቡን እራስ እቀጠቅጣለሁ! ገና ሥራውን አፈራርሳለሁ! በሥሙ ጉልበት እመታዋለሁ! ዕቅድ ሃሣቡን አፈራርሳለሁ! በኢየሱስ ሥም እመታዋለሁ! ዘወትር ምክሩን አበላሻለሁ!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection