Song Lyrics

ሲረዳኝ አይቼዋለሁ

Tadesse Mekuria
Tamagn New Egziabher
አዝ፦ ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲመራኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን እስከ ዛሬ የረዳኸኝ በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ ሁሉ በአንተ መች በራሴ? (4x) የአምላኬ ምሕረቱ በዝቶልኝ በቤቱ ዕድሜን ጨምሮልኝ ለትላንት ስሰጋ የነበርኩ አለሁኝ በጥላው ስለሆንኩ የረዳኝን አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲመራኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን እስከ ዛሬ የረዳኸኝ በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ ሁሉ በአንተ መች በራሴ? (4x) እጆቼን በክንዱ ደግፎ ጉልበቴን በክብሩ አጽንቶ መንፈሱን እጥፍ አድርጐልኛል በክብሩ ክብሩን ገልጦልኛል የረዳኝን አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲመራኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን እስከ ዛሬ የረዳኸኝ በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ ሁሉ በአንተ መች በራሴ? (4x) ሲማማል ጠላቴ ሊጥለኝ ቀንቶብኝ ጌታ ስላለኝ ቢወጣ ቢወርድ መች ይችላል? ኢየሱስ ለእኔ አጥር ሆኖኛል የረዳኝን አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲመራኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን እስከ ዛሬ የረዳኸኝ በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ ሁሉ በአንተ መች በራሴ? (4x) በሠልፉ እርሱ ተሰልፎ ተዋጊው እግዚአብሔር አልፎ የጠላት ከፍታው ተመቷል ለሥሙ ምሥጋና ይገባል የረዳኝን አመሰግናለሁ (2x) አዝ፦ ሲረዳኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያግዘኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲያቆመኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን ሲመራኝ አይቼዋለሁ ጌታን ኢየሱስን እስከ ዛሬ የረዳኸኝ በድካሜ ኃይል የሆንኸኝ በዝቶ ፀጋህ እዚህ መድረሴ ሁሉ በአንተ መች በራሴ? (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection