ሰው ሁኔታን አይቶ ይከዳል ጊዜን ጠብቆ ይርቃል ተስፋ እንደሌለው የማይተው ጌታዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው ዕውቀትን አይቶ ይከዳል አላፊ መሆኑን ዘንግቷል እያየ የአሁን የአሁኑን ረስቶ አወዳደቄን አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (2x) ዘለዓለም (2x) ትካዜዬን ለእርሱ ጥዬ የውስጤን መቃተት ጌታዬ ሰው እንኳን ቢከዳ ቢጥል እግዚአብሔር ግን ይረዳል ሃሳቤን የሚያውቅልኝ ድካሜን የሚረዳልኝ የውስጥ ጭንቀቴ የሚገባው እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው? አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (2x) ዘለዓለም (2x) አጽናኝ መስሎ ይጠጋል ጓደኛ መስሎ ይቀርባል ጠላትም በእርሱ ተጠቅሞ ብርሃኔንም አጨልሞ ግን የሚመካው የምጠጋው የልቤን የማጫውተው ድጋፍ መከታ የማደርገው እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው? አዝ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (2x) ዘለዓለም (2x)