ከባርነት ቀንበር ያወጣኸኝ እስራትን ፈተህ የለቀከኝ ምሥጋናዬን እንካ የእኔ ጌታ እንዳንተ አላየሁም የሚረታ የሕይወት ምንጭ ነህ ለተጠማ እንዲሁም ብርሃን በጨለማ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (2x) ቀንበርህ ያከበደው ለጫንቃዬ የነፍሴ ፈላጊ ባላንጣዬ እግዚአብሔር ከእግሬ ስር እስገዛልኝ እንድቀጠቅጠው እደረገኝ እግዚአብሔር ብርሃኔ መድሃኔቴ ሁሌ ከእኔ ጋር ነው በሕይወቴ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (2x) ማዳኑ በዛልኝ ቸርነቱ ከእኔ አላራቀም ምህረቱን ከመንፈሱ ዘየት እየቀባኝ በአደባባዩ አከበረኝ እዚህ ደርሻለሁና በጌታ አዜምለታለሁ ጠዋት ማታ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (2x) የነፍሴ ፈላጊ ጠላቶቼ የበረቱ አስጨናቂዎቼ በሞት ጥላ እንዳልፍ ፈረዱብኝ ግን ጌታ ታድጐ ሕይወት ሰጠኝ ሰልፍ ቢነሳብኝ ልቤ አይፈራም ጌታ ብርሃኔ ነው ለዘላለም (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኔቴ ነው (2x)