Song Lyrics

ርሆቦት

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
እስከሚያውቁኝ የተጣሉኝ ሁሉ አስፍቶኛል ጌታ እንደ ቃሉ እኔም በዝቻለሁ ደስ ብሎኛል ፍሬዬም አብቦ ይሄው ይታያል እንዲያ ያሳደዱኝ ጠላቶቼ ለመሆን ፈለጉ ወዳጆቼ እርሆቦት ጌታ ስላሰኘኝ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለኝ አዝ፦ ሮሆቦት (2x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል መሻቴንም ፈጽሞልኛል (2x) የገባልኝን ቃል እይፈጽምም ብዬ ተናግሬ ከቶ አይሆንም ባልኩኝ ጊዜ እግዚአብሔር ትቶኛል ርሆቦት ጌታ አስፍቶልኛል ዛሬ አቁሞኛል በተራራ አሳልፎ ያንን ሁሉ መከራ እኔም እነግራለሁ በረከቴን ያደረገልኝን መድሃኔቴን አዝ፦ ሮሆቦት (2x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል መሻቴንም ፈጽሞልኛል (2x) አሁን ግን ጽዋዬ ተርፎልኛል እስክረሰርስ ድረስ ሞልቶልኛል ከእንግዲህ በኋላ ከቶ አልጐድልም በረከት አድርጐኛል ለዚህ ዓለም የገባልኝን ቃል አይፈጽምም ብዬ ተናግሬ ከቶ አይሆንም ባልኩኝ ጊዜ እግዚአብሔር ትቶኛል ርሆቦት ጌታ አስፍቶልኛል አዝ፦ ሮሆቦት (2x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል መሻቴንም ፈጽሞልኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection