ትላንትና ለሊቱን በሥጋዬ ጥሬያለሁ አሁን ግን መረቦቼን በቃልህ እጥላለሁ የበረከት አምላክ ሆይ ስታዘዘው ቃልህን ተትረፈረፍኩኝ ዛሬ አይቻለሁ ሃይልህን (3x) አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ በዚህ ተራራ ታላቅ የሰባ ግብዣ እድርገህ በብዙ ታምራቶች በደመና ተገልጠህ ሌላውን አስክረሳ አስክመርጥ በዚህ መኖር በብዙ ባርከኸኛል እግዚአብሔር ሆይ ክበር (3x) አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ በትሬን ብቻ ይዤ ተሻገርኩ ዪርዳኖስን የሁለት ክፍል ሰራዊት አርገኸኛል ዛሬ ግን በጠላት ፊት ለፊት በዘይት ቀብተህ እራሴን ላመላለስከኝ ጌታ ምን እላለሁ ተመስገን (3x) አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ በዚያ ምድረ በዳ ላይ ብቻዬን ሳለሁኝ በድንገት ከአጠገቤ ምንጩ ፈለቀልኝ አለቆች እየቆፈሩ በቀራንዮ መስቀል ላይ የዘላለም ሕይወት ምንጭ ጌታ ኢየሱስ ኤልሻዳይ (3x) አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ በኤማኦስ መንገድ ላይ ተስፋ ቆርጠን ሳለን ኢየሱስ እራሱ ቀድሞ ይህን ቀን አብሮ ሆነ የልብን ሃዘን ነቅሎ ለሚሞላን በደስታ ምሥጋና ያንስብናል ለአምላካችን ለጌታ (3x) አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ መስሎኝ ነበረ ለእኔስ በጠላቴ የተረታሁ አቀበት ቁልቁለቱን ከቶ የማልወጣው ከፍጥረት የታወቀው በድንቅ በታምራቱ በብዙ ጥንቃቄው ጠብቆኛል በቤቱ አኑሮኛል በቤቱ አክርሞኛል በቤቱ አዝ፦ ስለዚህ ሁልጊዜ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ላይ ሌላ ጨምራለሁ በጥሩ የዜማ ቃል ፊትህ እጫወታለሁ አምላኬ ጌታዬ አመሰግናለሁ አምላኬ ጌታዬ ከፍ አደርግሃለሁ