Song Lyrics

ጽዮን ሆይ ተነሺ

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
የምሬት ጊዜ የአምባ ጊዜሽ ያንን መከራ ጉስቁልናሽ ተመልክቶታል በቃ አታልቅሺ ዘምሪ ዕልል በይ ጽዮን ተነሺ (2x) ጽዮን ሆይ ተነሺ አዝ፦ ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ የ እግዚአብሔር ጆሮዎች ጸሎትሽን ሰምተዋል አንቺን ለማዳን እጁን ዘርግቷል ያንን መከራ የሚያስረሳሽ ይዞልሽ መጥቷል ድንቅ በረከቱን (2x) አዝ፦ ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ ትላንት በለቅሶ ለዘራሺው ዘርሽ መጥቶልሻል ጌታ በሳቅ ሊያሳጭድሽ ያኔ በመከራሽ የገባልሽን ቃል ጌታ ሊፈጽመው ከማደሪያው ነቅቷል (2x) አዝ፦ ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection