ነገ በሕይወትህ ድንቅ አደርጋለሁ ብቻ አንተ ተቀደስ እኔ ሰራለሁ ብሎ ጌታ አሰበኝ ቃሉን አክብሮ ምርኮዬን መልሷል ስሜን ቀይሮ አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል ጌታውን ተማምኖ የሚጠባበቅ ኃይሉ ታደሰ እንጂ ዘላለም አይወድቅ እግዚአብሔር ይሄ ነው ተስፋ ያረኩት ጸሎቴን መልሷል ኑ ስሙን ባርኩት አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል በለስን ጠብቆ ፍሬን የበላ ከጌታው ጋር ሆኖ ያልቀረ ኋላ አከናውኖልኛል ምኔን ልክፈለው የሚል በዕልልታ ጌታን ያክብረው አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል ሥጋዬን በጥርሴ እነክሳለሁኝ ቢገድለኝም እርሱን እጠብቃለሁኝ ብሎ ለጠበቀው ጌታን በእምነት ሁለት እጥፍ መጣ የኢዮብ በረከት አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል እረድኤቴና መድሃኒቴ አከናውኖልኛል ኢየሱስ አባቴ በፊቱ ዘላለሁ እንደ እንቦሳ ስላራቀው ከእኔ ያንን አበሳ አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል ልጄ ልብህን ስጠኝ ወደ እኔ ና እሰራለሁ ብሎ አባበለና እኔም ከአምላኬ ጋር ወዲያው ስታረቅ ጸሎቴን መለሰው ሥሙ ይባረክ አዝ፦ እግዚአብሔርን ጠብቄ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ተወስዶ በዛው አልቀረም በጊዜው ኢየሱስ መልሶልኛል ሥሙ ይባረክ ይንገሥ አሰኝቶኛል (2x)