Song Lyrics

መፈታቴን አውጃለሁ

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
ችግር መከራዬን ብሶቴንም ልውጣው የሚረዳኝ የለም ከእኔ አትራቅ ለአንድ አፍታ ከልቤ ይሄንን ብነግረውን ቀኜን ያሰረውን ገመዴን በጠሰው (2x) አዝ፦ መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን ኃይለኛና ታላቅ ነገር አደርጋለሁ በእውነት የታመነ ቤትን እሰራለሁ ታማኙ አምላኬ እንደተናገረው በእርግጥ አድርጐታል ስሙን አከብራለሁ (2x) አዝ፦ መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን ናቡከደነጾር የተባለው ንጉሥ ዓይኖቹን አንስቶ ከሰራዊት ቅዱስ ባቢሎንን አይቶ በትዕቢት ታሰረ ለሰባት ዘመናት ምድረ በዳ ቀረ ዓይኖቹን አንስቶ እግዚአብሔርን ሲያየው ወደ ቀድሞው ሕይወት ለክብር መለሰው ይህንን ላደረገው ለታላቁ ጌታ ምሥጋናን እንስጠው በዕልልታ በሆታ (2x) አዝ፦ መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን እስራትን ፈቶ ቀንበር የሰበረ በሰማይ በምድር በጣም የከበረ ፍጥረታት በሙሉ ሚታዘዙለት ለበጉ ለኢየሱስ ክብር ይሁንለት (2x) አዝ፦ መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection