ሕዝቡን ከኃጢአት ሚያድን ሚፈውስ ድንቅ መካር ኃያል ስሙም ኢየሱስ የእስራኤል መሪ ታላቁ መስፍን በቤተልሄም ተወለደልን (2x) አዝ፦ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ አሜን ሰባሰገል መጡ ከነበሩበት ለተወለደው ህጻን ሊሰግዱለት የአዲስ ኪዳን በግ ታላቁ ጌታ ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊፈታ ሊሆን ደስታ አዝ፦ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ አሜን ዝማሬ በመላእክት አስተጋባ እጣንና ከርቤም በበረት ገባ በምድር ቅጥርም ውስጥ ጽድቅም ይሆናል እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ወዷል (2x) አዝ፦ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ አሜን ታናሽ ከተማ ቤተልሔም ሆይ መድሃኒት ከአንቺ ወጥቶ የለም ወይ ክብር ምሥጋና ውዳሴ ስግደት ለህጻኑ ኢየሱስ እናቅርብለት (2x) አዝ፦ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ አሜን ኮኮብ ይወጣል በትር ይነሳል ለእስራኤል መዳን ይሆንለታል ተብሎ ተነግሮ ነበር አሁን ግን ሆኗል አምላክ ከሕዝቡ ጋራ ሊታረቅ ወዷል (2x) አዝ፦ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ ከተማ ለዓለም የምሥራች ከአንቺ ዘንድ ተሰማ አሜን