አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (2x) አናልፈውም ብለን አለፍነውን የመከራው ዓይነት ብዙ ነው መች ተሸንፈን እናውቃለን አሸናፊዎች እንበልጣለን ይህ ያልፋል ብለን ያልገመትነው የእኛ ታሪካችን ብዙ ነው እያለፍን በድል ጐዳና አሸበረቅን በምሥጋና አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (2x) በሃሩር ጊዜ ሆኖ ጥላ በፍላጻ ሁሉ ከለላ ልጆቹን ፊት ፊት እየመራ ደርሰናል ጺዮን ተራራ የድካሙ ጊዜ አብቅቶ በብርታት ሕይወት ተተክቶ በሽብሸባ ፊቱ ዘለናል እስካሁን ድረስ ረድቶናል አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር አሁን ከእኔ ጋራ ያላችሁ አቤኔዘር የሆነላቹህ በፊቱ ቅረቡ በዕልልታ ሥሙ ይባረክ የእኛ ጌታ ከአመድ ከትቢያ ያነሳቹህ በዚህ ጉባኤ ስንቶች ናችሁ ታዲያ ለምን ነው ዝምታ የታል ደስታችሁ ለዚህ ጌታ አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር ይህ ያልፋል ብለን ያልገመትነው የእኛ ታሪካችን ብዙ ነው እያለፍን በድል ጐዳና አሸበረቅን በምሥጋና እንዲያ ሚከሰን ጠላታችን አሁን የታለ ከፊታችን ኢየሱስ ስለነገሠ በጠንካራው ክንድ ተደቆሰ አዝ፦ አቤኔዘር አቤኔዘር እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል እንደተለመደው ድንቅ አድርጐልናል ባሕሩንም ከፍሎ አሻግሮናል አቤኔዘር (3x)