Song Lyrics

የታረደው በግ

Tadesse Eshete
Yetaredew Beg
አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x) አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x) መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረካቸው በምድርም ላይ ይነግሳል እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ [1] መጽሐፉን ወስዶ ማኅተሙን ፈቶ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅቶ ለአምላክ መንግሥት ካህናት ሆንን በበጉም ስራ ተመሰገንን አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x) በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ በረከትና ክብር ምሥጋናም ኃይልም ከዘለዓለም እስከዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ [2] በሰማይ በምድርም ከምድርም በታች በእነርሱም ውስጥ ያለን ፍጥረታት ከዙፋኑ ፊት እንወድቃለን ለበጉም ክብር እንዘምራለን አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x) አየሁም በዙፋኑም በእንስስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምጽ ሰማሁ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋት እና ሺ ጊዜ ሺ ነበረ በታላቅም ድምጽ የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጠብብም ብርታትትም ክብርም ምሥጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ [3] እልፍ አእላፋት ብዙ መላእክት ለታረደው በግ እሚሰግዱለት እስከዘለዓለም ለሚኖር ጌታ ቅኔ ሲቀኙ ጥዋትም ማታ አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x) ከሽማግሌዎቹም አንዱ ተመልሶ እንዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው ከወዴትስ መጡ አለኝ እኔም ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አልኩት አለኝም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል ከእንግዲህ ወዲስ አይራቡም ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም ፀሐይም ትኩሳትም ሁሉም ከቶ አይወርድባቸውም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና እግዚአብሔርም እምባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል [4] ከታላቅ መከራ የመጡ ናቸው በበጉ ደምም አነጹ ልብሳቸውን በዙፋኑ ፊት ሌት ተቀን አሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ አዝ፦ በረከትና ክብርም ጥበብም ባለጸግነት ኃይልም ብርታትም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለነበረው ላለው ለሚመለሰው ለታረደው በግ ምሥጋና ይድረሰው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection