Song Lyrics

መሸሸጊያ ዋሻ

Tadesse Eshete
Yetaredew Beg
መሸሸጊያ ዋሻ /2 መከታ ጋሻችን/2 ጦራችን አንተ ነህ/2 ጠላትን መውጊያች/2 አንተም ተዋጊ ነህ ስምህ እግዚአብሄር ነው እንኮራብሃለን ደስታህ ኃይላችን ነው። (x2) ከግብፅ ባርነት ከፈርዖን ግዛት ብርሃን ጨልሞ ሞት ከሰፈነበት ልጆችህ ሲጮሁ ባርነት መሯቸው አንተ ነህ ተዋግተህ ነፃ ያወጣሃቸው/2። በብዙ በጥቂት ማዳን የማይሳንህ ፈጥነህም የምትደርስ ስምህን ለሚጠሩ ድብቅ ጦር አንተ ነህ ጠላት የምትመታ እንመካብሃለን የእኛ መከታ/2። ጠላትም ቢመጣ ጦርን አስከትሎ በሠረገላው ብዛት ጉልበታችን ዝሎ ዓይናችንን ከፍተህ በእምነት ብናየው ከጠላት የሚበልጥ ድብቅ ጦር ነው ያለው/2። ካቻምናን ስንፈራ ለአምናው አድርሶናል አምናንም ስንፈራ ዘንድሮ አድርሶናል ዘንድሮን ስንፈራው ደረስን አሁንን ታድያ ምን አሰጋን የወደፊቱን/2።
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection