Song Lyrics

በቀራንዮ ያደረገልኝ

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
ስለት ነበረብኝ ለኢየሱስ ለጌታ እንዲህ ካረገልኝ እስራቴን ከፈታ እንደመልካም አባት አንጀቱ ራርቶ አይዞህ ልጄ አለኝ ሳልጮህ ገና ሰምቶ (2x) ሃጥያት እየሰራሁ እንዲያ እያደከምኩት የመስቀል ላይ ጣሩን እየዘነጋሁት ምህረት ቸርነቱ ግን ይከታተሉኛል አባብለው አምጥተው ቤቱ ያገቡኛል ፊቱ ያቆሙኛል አዝ፦ በቀራንዮ ያደረገልኝ ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ ከአቻምና አምና ከአምና ዘንድሮ የጌታ ውለታ አያልቅም ተቆጥሮ የምህረቱ ብዛት የፍቅር ጥልቀቱ ከልቤ ውስጥ ገባ የእግዚአብሔር ምህረቱ የጌታ ምህረቱ የፍቅር ዓይኖቹን በእኔ ላይ ያቀና በምክር እግሮቹን ወደኔ ያቀና እጆቹን ዘርግቶ ባርኮኛልና ይኸው መስዋእቴ ከነፍሴ ምሥጋና ከልቤ ምሥጋና አዝ፦ በቀራንዮ ያደረገልኝ ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ የሚያስጨንቀኝን ከሳሼን አዋርዶ ሳልመርጠው የመረጠኝ ሳልወደው እጅግ ወዶ ከአባቱ ጋር ስፍራን የሚያዘጋጅልኝ ባለውለታዬ ኢየሱስ ይክበርልኝ ጌታ ይክበርልኝ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ጌታን አክብሩክኝ እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሉ ዘምሩልኝ የጌታ ውለታ መግለጫ ያላችሁ እስኪ እናምልከው ዕልል እያላችሁ ክበር እያላችሁ አዝ፦ በቀራንዮ ያደረገልኝ ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ (2x) እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡ ለአንድ አፍታ እናንተን ለማዳን ስለሞተው ጌታ በቀራንዮ መስቀል ላይ የተንጠለጠለው ከዘላለም ጥፋት አንተን ለማዳን ነው አንቺን/እኛን ለማዳን ነው (2x) አዝ፦ በቀራንዮ ያደረገልኝ ከሁሉ በላይ ትዝ እያለኝ ከቅዱሳን ጋር እሰግዳለሁ በአዲስ ዝማሬ አዜማለሁ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection