ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈጠናቸው ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ ከእዛ ጉስቁልና ከመከራ ወጣ (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች እርሷም እንደሰው . (1) . ዘመኗ ደረሰ እምባዋ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ ዛሬም ብንጠበው በመጠበቂያችን እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን (2x) አዝ፦ አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ ውልህን ትገልጻልህ