ብዙ አመታት ከእኔ ጋራ ስትወጣ ስትወርድ ስለ ስሜ ስትሰደብ ስትመታ ስትዋረድ ልመጣ ስል ትንሽ ሲቀር ልጐበኝህ ልፋትህን ከንቱ አድርገህ ምነው ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ አፍርተህ እንዳገኝህ ስትተጋ ስጐበኝህ የድካምኽን የልፋትህን እንደከፍልህ ዋጋህን እንደጀመርክ ብትጨርስ ያን ፍቅርህን ነፍሳት ለማዳን የነበረህን ጥማትህን ስትዘምር ስትጨልይ ጊዜህን ሰጥተህ ልሸልምህ ልመጣ ስል ምነው ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ አፍርተህ እንዳገኝህ ስትተጋ ስጐበኝህ የድካምኽን የልፋትህን እንደከፍልህ ዋጋህን የጸለይከውን ጸሎትህን ልመናህን ላብሰው ስል ያነባኸውን እንባህን በአባትነት ፍቅር ልጄ ብዬ ስጠራህ ከቦታው አሁን እጄን እዘረጋለሁ አዝ፦ ፍሬ አፍርተህ እንዳገኝህ ስትተጋ ስጐበኝህ የድካምኽን የልፋትህን እንደከፍልህ ዋጋህን ከአዳኝ ወጥመድ የዘለልከው የወጣኸው እንደ ቃዬል ፍቅሬን ኃይሌን የቀመስከው እኔ ነበርኩኝ ውበትና ደም ግባትህ ልመጣ ስል ይሄን ረስተህ ምነው ሸሸህ አዝ፦ ፍሬ አፍርተህ እንዳገኝህ ስትተጋ ስጐበኝህ የድካምኽን የልፋትህን እንደከፍልህ ዋጋህን