Song Lyrics

የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጽ

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
የምትወደው ልጅህን ወደ ተራራ ውሰደው በእዚያም ለእኔ ክብር መስዋዕት አድርገህ ሰዋው ጌታ እንዲህ ይለኛል ብዬ ከቶ አልጠበኩም ቢሆንም ሳስተያየው ከእርሱ ፍቅር አይበልጥም እኔም ሳላወላውል ወደዚያ ስፍራ ደረስኩኝ ልጄን ለመሰዋት መሰዊያውን ሰራሁኝ እንጨትም ረበረብኩኝ ልጄን ይስሐቅ አሰርኩኝ በዚያም አጋደምኩኝ እጄንም ዘረጋሁኝ ድምጹ ከሰማይ መጣ ሲል እጅህን አትዘርጋ አብርሃም እንደምትወደኝ በእውነት ዛሬ አየሁኝ የእውነት በረከትን እባርክሃለሁኝ ልጅህን ላልከለከልከኝ በራሴ ምላለሁኝ አዝ፦ የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ ፈርዖን ሲያሳድደኝ ዳግም ባሪያው ሊያደርገኝ በሰረገላው ብዛት በሰልፉ ሲነሳብኝ ቀይ ባሕርም ከፊቴ ሞልቶ ተደቅኖብኝ ማለፊያ መንገድ ጠፍቶኝ በፍርሃት ተሞላሁኝ ጌታ ግን ቃሉን ሰጠኝ ብርሃኑን አበራልኝ ባሕሩን እንድትከፍለው በትርህን አንሳ አለኝ እኔም ለቃሉ ታዘዝኩ በጌታ ላይ ተደገፍኩ ባሕሩም ተከፈለ ጠላቴም ሰጥሞ ቀረ አዝ፦ የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ ከብዙ የጠላት ሴራ እኔ ነኝ ያተረፍኩህ እንድታገለግለኝ ልቤን በአንተ ያሳረፍኩኝ ብሎ እንደታማኝ ባሪያ ጌታ ስለቆጠረኝ ወደ ነነዌ እንድሂድ መለዕክትን ሰጥቶ ላከኝ እኔ ግን በምትኩ ተርሴስ ልሄድ ፈለኩ ብዙ ዋጋ ከፈልኩ በመርከብ ተሳፈርኩ እንዳልሰማ እየሆንኩኝ በፊትህ ኮበለልኩኝ ቃሉን በመተላለፍ እግዚአብሔርን በደልኩኝ እርሱ ግን መቼ ተወኝ አምርሮ ተከተለኝ ነፋሳትን አዘዘ ማዕበሉን አስነሳብኝ እንዲያውም ይባስ ብሎ ከባሕር ውስጥ ተጣልኩኝ ሶስት ቀንና ሌሊት በዓሣ ሆድ አደርኩ በመከራዬ ሳለሁ ወደእግዚአብሔር ጮህኩኝ ይልቁንም በንስሃ ከእርሱ ጋር ተስማማሁ ጌታዬም ይቅር አለኝ ዳግም ተጠቀመብኝ ነነዌንና ጌታን ለማስታረቅ በቃሁኝ አዝ፦ የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምጼን መጽናናት ሲያቅተኝ በፊትህ ያለቀስኩትን እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ተመለከተኝ ድምጹንም አሰማኝ እንዲህ አለኝ ዓይንህን ከእንባ ከልክል ድምጽህንም ከለቅሶ በጣም ቶሎ ታያለህ እንባህ ከዓይንህ ታብሶ ኦሆሆ ኦሆሆ ኦሆሆ ምርኮህም ተመልሶ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection