Song Lyrics

እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅም

Tadesse Eshete
Mefetaten Awujalew
ብዙ ተዓምራቶችን ሲሰራ ያያችሁ ሁልጊዜ በቃሉ እንዲህ ሲናገራችሁ ማነው እንደ ኢየሱስ/ጌታ የሚሆንላችሁ በመከራው ጌዜ ከእርሱ የሸሻችሁ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና የመረጠህ አምላክ አይተውህምና አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና ቅዱሳኖች ጽኑ ጨለማው ይነጋል ኢየሱስ ሲያስበን ሁሉም ነገር ያልፋል ፀሐይ ሲወጣበት ተኖ እንደሚጠፋ ቀናችን ይሄዳል ያስቆረጠን ተስፋ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና የመረጠህ አምላክ አይተውህምና አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና እግዚአብሔር ከልቡ አያስጨንቀንም ሕዝቡን ለተኩላዎች አሳልፎ አይሰጥም ቢያሳዝነን እንኳን ልቡ ሚራራ ነው ከእርሱ ጋራ መስማማት ያ ነው የሚሻለው (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና የመረጠህ አምላክ አይተውህምና አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና ክለቅሶ ከሃዘን ከማማረር ሕይወት ክውድቀት ከድካም ፈጥኖ ሚያነሳበት የጠፉትን ሁሉ የሚፈልግበት እግዚአብሔር ጊዜ አለው የሚጐብኝበት (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና የመረጠህ አምላክ አይተውህምና አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection