የእግዚአብሔር ጊዜ የተወደደ ደረሰ ለእኔ እርሱ የፈቀደው የማጨድ ጊዜ የመከር ዘመን መጥቷል ከፊቴ የመከናወን (2x) እግዚአብሔር ያለው ይሆናል አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (2x) ዘመን መጣ ለእኔ (8x) ያላየሁትን ባይኔ የማይበት ያልሰማሁትን የምሰማበት በህልውናው ምጥለቀለቅበት ክብሩን እያየሁ የማመልክበት (2x) ይሆናል ያለው ይሆናል አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (2x) ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (2x) ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ መንፈሱ መጣ ከላይ ከላይ (2x) ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (2x) ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ አባቴ መጣ ከላይ ከላይ (2x) እኔ የሚገርመኝ እኔ የሚደንቀኝ ይህ ግዙፍ ሰማይ ይህ ግዙፍ ምድር ሌላ አልተናገርክ ሌላ አላልካቸው በአንድ ቃል ብቻ አጸናሃቸው (2x) እግዚአብሔር ያለው ይሆናል አትችልም አይሆንም የሚለው የታል (2x) ሌሊቱን ሙሉ ቢጥር ቢደክም መረቡ ባዶ ዓሣ የለውም ኢየሱስ መጥቶ ካልተናገረው ፈቀቅ በልና ወደጥልቁ ጣለው (2x) እንዳለው መረቡ ሞላ ተዐምር ነው ድንቅ ነው የሰራው ስራ (2x) ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (2x) ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ መንፈሱ መጣ ከላይ ከላይ (2x) ከላይ ከላይ ከላይ ከላይ (2x) ምህረቱን ለእኔ ሊያሳይ አባቴ መጣ ከላይ ከላይ (2x)