አዝ፦ ጠቢባኖች አዋቂዎች ተምረናል ያሉ ኃይልህን ለማወቅ ግን ከቶውን አልቻሉም ለደካማው ለታናሹ ጥበብን ሞላኸው በኖረበት ምድር ሞገስ ሞገስ አለበስከው መች በራሴ በጉልበት እኔ እዚህ መድረሴ አውቀዋለሁ በኢየሱስ ነው ያማረው ሕይወቴ (2x) አሁንማ በዛ በዛ ቸርነቱ ተቆጥሮ አይዘለቅ የጌታ ምህረቱ የእርሱ ቸርነቱ (2x) ከእግዚአብሔር በቀር ሰው እንዴት ይኖራል ሲወጣ ሲገባ በማን ይታመናል ኧረ እኔስ አይሆንልኝ ያለ ጌታ ከቶ አልውልም አላድርም ስሙን ሳልጠራ ቅር ቅር ቅር ይለኛል አባቴ አይደለ እርሱ ይርበኛል ይናፍቀኛል ድምጹ ምግቤ ነው ያበረታታኛል ኢየሱስ ለኔ ሞገስ ሆኖኛል ስሙን ስጠራ እጅግ ያኮራኛል ማይነቃነቅ ጽኑ ግንብ ሆኖኛል እውነት ነው የምትሉ ፍቅር ነው የምትሉ ጌታ ነው የምትሉ ከኔ ጋር እልል በሉ እውነት ነው የምትሉ ጌታ ነው የምትሉ አባት ነው የምትሉ ከኔ ጋር እልል በሉ አዝ፦ ጠቢባኖች አዋቂዎች ተምረናል ያሉ ኃይልህን ለማወቅ ግን ከቶውን አልቻሉም ለደካማው ለታናሹ ጥበብን ሞላኸው በኖረበት ምድር ሞገስ ሞገስ አለበስከው መች በራሴ በጉልበት እኔ እዚህ መድረሴ አውቀዋለሁ በኢየሱስ ነው ያማረው ሕይወቴ (2x) አሁንማ በዛ በዛ ቸርነቱ ተቆጥሮ አይዘለቅ የጌታ ምህረቱ የእርሱ ቸርነቱ (2x) ከእግዚአብሔር በቀር ሰው እንዴት ይኖራል ሲወጣ ሲገባ በማን ይታመናል ኧረ እኔስ አይሆንልኝ ያለ ጌታ ከቶ አልውልም አላድርም ስሙን ሳልጠራ ቅር ቅር ቅር ይለኛል አባቴ አይደለ እርሱ ይርበኛል ይናፍቀኛል ድምጹ ምግቤ ነው ያበረታታኛል ኢየሱስ ለኔ ሞገስ ሆኖኛል ስሙን ስጠራ እጅግ ያኮራኛል ማይነቃነቅ ጽኑ ግንብ ሆኖኛል እውነት ነው የምትሉ ፍቅር ነው የምትሉ ጌታ ነው የምትሉ ከኔ ጋር እልል በሉ እውነት ነው የምትሉ ጌታ ነው የምትሉ አባት ነው የምትሉ ከኔ ጋር እልል በሉ አምናም ስገረም ስደነቅ ዘንድሮ መጣ በእጥፍ ከርሱ ጋር መሆን ተስማምቶኛል እንደ መህልቅ ፍቅሩ ይዞኛል ወዲህ ወዲያ አልል ተመችቶኛል (2x) ምቹ ነው የምትሉ አባት ነው የምትሉ እንደ እናት ነው የምትሉ ከኔ ጋር እልል በሉ (2x)