ከማመስገን ፈጽሞ እኔ አልቆጠብ ልጅ ብቻ መሆኔ ይበቃኛል እርሱን ለማመስገን አልናወጥ በሆነው ባልሆነው ነገር እርሱ ያለው ይሆናል አንዳችም ሳይቀር (3x) እርሱ ያለው (አሃ)ጌታ ያለው (ኦሆ) ውዴ ያለው (አሃ) አባ ያለው (ኦሆ) እርሱ ያለው ይፈጸም ሌላው (3x) ሌላው ከንቱ ነው እርሱ ያለው ይፈጸም ሌላው (3x) ሌላው አላፊ ነው አዝ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር እንዲና እንዲያ እናደርጋለን ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (3x) ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ሁሉም ከንቱ ነው ከንቱ ከእግዚአብሔር በቀር የተጣበቀ ከዚህ ጌታ ጋር ዘመኑ ሁሉ ይለመልማል (2x) አዝ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር እንዲና እንዲያ እናደርጋለን ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (3x) ወደ ግራ እኔ ወደ ቀኝም አልል በቀን በሌት አዎ ቃሉን ነው የማስብ የዚያን ጊዜ መንገዴ ይቀናልኛል የረገጥኩትን ሁሉ እርሱ ያወርሰኛል (2x) አዝ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖር እንዲና እንዲያ እናደርጋለን ብሎ ማረፍ መልካም ነው በርሱ መታመን አያዋጣም መሯሯጥ እዚህም እዚያም ማለት (3x)