Song Lyrics

እግዚአብሔር አንተ

Solomon Yirga
Meazaye Neh
አዝ፦ እግዚአብሔርን አንተ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ አምባዬና መሸሸጊያዬ ነው ኢየሱስ በእርሱ እታመናለሁ ኢየሱሴን ኢየሱሴን በጣም እወደዋለሁ (2x) እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም አድኖኛል እውነት እንደጋሻ ሆኖ ዙሪያዬን ከቦኛል መድኃኒት መድኃኒት እርሱ ሆኖልኛል (2x) በቀንም ከሚበር ከሌሊትም ግርማ አድኖኛል በመንገዴ ሁሉ ስለኔ መላእክቱ ታዘዋል ጥበቃው ጥበቃው እንዴት ያስተማምናል (2x) አዝ፦ እግዚአብሔርን አንተ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ አምባዬና መሸሸጊያዬ ነው ኢየሱስ በእርሱ እታመናለሁ ኢየሱሴን ኢየሱሴን በጣም እወደዋለሁ (2x) በተኩላና በእባብ ላይም እጫማለሁ አንበሳ ዘንዶውን እረጋግጣለሁ በርሱ ተማምኜ ሁሉንም አልፋለሁ ስሙንም ደግሜ ደግሜ እጠራለሁ (2x) ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ኢየሱስ በጣም እወደዋለሁ ኢየሱስ ኢየሱስ በጣም እወደዋለሁ ኢየሱስ ሃሌሉያ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection