ምንም ክፍያ አልከፈልኩም ከላይ ወደታችም አላልኩም በጓደኛም ዘመድ አልመጣሁም ጌታን ለማግኘት አልደከምኩም በፍቅር ቃሉ ሲናገረኝ እወድሃልሁ ብሎ ሲለኝ እጅግ ተገረምኩ ተደነቅኩ እንዲህ ያለ ሰው ማነው አልኩ ያለ የነበረ የሚኖረው ኤልሻዳዩ ጌታ ለካስ (3x) ለካስ ኢየሱስ ነው ሁሉን ቻይ ጌታ ለካስ ለካስ ኢየሱስ ነው ይገርማል ኧረ እንዴት ይገርማል ይደንቃል ኧረ እንዴት ይደንቃል ሳልመርጠው ኢየሱስ መርጦኛል ሳልወደው እንዲህ ወዶኛል ከሞት መካከል ነጥቆ አውጥቶኛል አዝ:- ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ያደረገልኝን እያየሁ አምኜ በድንገት ያገኘሁት ሕይወቴን ሁሉ የሰጠሁት ይኸው እስካሁን ይመራኛል ደግሞም ዘላለም ያኖረኛል ከእጆቹ መሃል ማን ያወጣኛል ከእጁ ፈልቅቆ ማን ይወደኛል ይበልጣል ከሁሉም ይበልጣል ይመረጣል ኢየሱሴ ይመረጣል መች አሳልፎ ይሰጣል ስሙ ከስሞች ይበልጣል ኢየሱን ጠርቶ ማን አፍሮ ያውቃል አዝ:- ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ያደረገልኝን እያየሁ (2x) የክብር ጌታ ድንቅ አረገ አቤት ዲያቢሎስ ተናደደ ውስጠ ሚስጥሩም ተገለጠ የጋረደውም ተቀደደ አሁን ምን ይበል ምን ይዋጠው ኢየሱስ ማንነቱን ሲገልጠው (2x) ይነድዳል እሳቱ ይነድዳል ይዋረዳል ዲያቢሎስ ይዋረዳል መች በዚህ ብቻ ያበቃል የያዘውን ሁሉ ይለቃል ማሳወር እንጂ እሱ ማብራት የት ያውቃል ማዋረድ እንጂ እሱ ማክበር የት ይውቃል አዝ:- ሳመሰግነው ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ስዘምርለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ እልል ስልለት ብውል ታዲያ መች እጠግባለሁ ያደረገልኝን እያየሁ (2x) እስኪ እንደኔ ጌታ የሰራላችሁ በምድረ በዳ ውሃ የሰጣችሁ ይሰማ ዛሬ እልልታችሁ ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ (ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ) እስኪ እንደኔ ጌታ የሰራላችሁ በጨለማ ውስጥ ብርሃን የሆናችሁ ይሰማ ዛሬ እልልታችሁ ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ (ፈጽሞ አይቆጠብ ድምጻችሁ)