እውነቱ አዳነኝ እውነት ነው ፈልጐ አገኘኝ ፍቅር ነው አደራረጉ ልዩ ነው ከምንገምተው በላይ ነው (2x) እኔ ልናገር ተደርጐልኛል ቀንበሬም በርሱ ተሰብሮልኛል አርነት ወጣሁ ነፃ አውጥቶኛል ከዚያች ሩጫ እኔን ፈቶኛል የተፈታ ሰው የተለቀቀ መውጣት መግባቱ የተጠበቀ ያመሰግናል ያመሰግናል ጊዜው ሁኔታ መች ያስቆመዋል ያመሰግናል ያመሰግናል ማግኘት ማጣቱ መች ያስቆመዋል ያኔ በልጅነት ገና መጀመሪያ ጌታ ተናገረኝ በኔ እንደሚሰራ የተናገረው ቃል ጊዜውን ጠብቆ ሲፈጸም በዓይኔ አየሁ ጌታ አይረሳም እኮ (2x) አንድ የገባኝ ነገር የተረዳሁት እንደማይረሳ ነው በዘመኔ ያየሁት አንድ የገባኝ ነገር የተረዳሁት እንደማይጥል ነው በዘመኔ ያየሁት አንድ የገባኝ ነገር የተረዳሁት ረዳት መሆኑን ነው በዘመኔ ያየሁት አንድ የገባኝ ነገር የተረዳሁት አባት መሆኑን ነው በዘመኔ ያየሁት እውነቱ አዳነኝ እውነት ነው ፈልጐ አገኘኝ ፍቅር ነው አደራረጉ ልዩ ነው ከምንገምተው በላይ ነው (2x) ብለው አይበቃኝ ረዳት ብለው አይበቃኝ አባት ብለው አይበቃኝ ፈዋሽ ብለው አይበቃኝ ፍቅር ብለው አይበቃኝ ልዩ ብለው አይበቃኝ ልዩ (2x) እርሱ ከሁሉም በላይ ነው እርሱ ከሁሉም በላይ ነው እርሱ የጌቶች ጌታ ነው እርሱ የአማልክት አምላክ ነው (2x)