Song Lyrics

ስላንተ ቢወራ

Solomon Yirga
Meazaye Neh
አዝ፦ ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን ቃላት አይገልጸውም ያረከውን ነገር (2x) ሞቴ በሕይወት ተቀይሮልኛል ኑር ብለህ ፈቅደህልኛል በምድር በርዝመቷ በስፋቷ በላይ በላይ በከፍታ እንድወጣ እንድገባ ፈቅደህልኛል የሚይዘኝ የለም ከፊቴ ወጥተህልኛል (2x) አዝ ፦ ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን ቃላት አይገልጸውም ያረግከውን ነገር (2x) አርነት ነፃ ወጥቻለሁ እርሱ ለቅቆኝ ተለቅቄያለሁ አልሄድ ወደኋላ ወደፊት እራመዳለሁ እርሱ ከከፈተው አትገባም የሚለኝ ማነው ሸክሜን ጣለ ቀንበሬን ሰበረ እዳዬም በርሱ ተከፈለ አለኝ አልጥልህም አልተውህም ፍጹም ከእጄ አላወጣህም መርጬሃለሁ ምንም ነገር አያስፈራህም አዝ፦ ስላንተ ሲወራ ሲነገር ቢዋል ቢታደር የሚበቃ አይደለም ብዙ ነው ያረከው ነገር እንዲሁ ብቻ ልበል ተመስገን ቃላት አይገልጸውም ያረከውን ነገር (2x) እየገባኝ መጣ አሁን እየተረዳሁ ነገሬ ሁሉ ባንተ ሰምሮ እያየሁ አጋጣሚ አይደለም ለካ ከላይ ታዞ ነው አርፌ እንድኖር ቀድሞ ስራዬን ሰርቶት ነው ከተመስገን ሌላ ታዲያ የምለው ምንድነው ተመስገን (4x) የኔ ጌታ ተመስገን ተመስገን ላረግክልኝ ነገር (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection