Song Lyrics

አሳርፈኽኛል

እንዲህ አልነበረም ታሪኬ አንተ ሳትገባ በሕይወቴ (2x) ውስጤን ስትነካው ታወቀ በፊቴ አሳርፈኸኛል ኢየሱስ መድኃኒቴ (2x) አንተ ነህ ትምክህቴ ውበት ደም ግባቴ አመሰግናለሁ ተመስገን አባቴ (2x) ምህረትህ ቸርነትህ ሁልጊዜ ይከተሉኛል ዘለዓለም በቤትህ ያኖሩኛል (2x) እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝ አንድም ነገር የለም በለመለመው መስክ ይመራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ያሳድረኛል ነፍሴን መለሳት ስለስሙ በጽድቅ መንገድ መራኝ በሞት መሃከል እንኳን ብሄድ እርሱ ከእኔ ጋር ነውና ክፉን አልፈራም እኔ አልፈራም ለእኔ ያደረገው የሆነው ይህ ነው አይባልም ብዙ ነው (2x) እኔ ነፃ እንድሆን ሁሉን ሆኖልኛል ሞቴንም በሞቱ ጌታዬ ለውጧል (2x) አንተ ነህ ትምክህቴ ውበት ደም ግባቴ አመሰግናለሁ ተመስገን አባቴ (2x) ምህረትህ ቸርነትህ ሁልጊዜ ይከተሉኛል ዘለዓለም በቤትህ ያኖሩኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection