ሰማይን ይሁን ያለው ማነው እግዚአብሔር ነው ምድርን ይሁን ያለው ማነው የእኔ አባት ነው ታዲያ እኔ ለምን እጨነቃለሁ ዝም ብዬ እዘምራለሁ አሃ ታዲያ እኔ ለምን እጨነቃለሁ በደስታ እዘምራለሁ አሃ እርሱ ተናግሯል በሕይወቴ ላይ የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል ጌታ ተናግሯል ቤተሰቤ ላይ የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል ጌታ ተናግሯል በሃገሬ ላይ የሚቀር የለም ሁሉም ይሆናል እግዚአብሔር በማን ይመሰላል ከማን ጋራ ይወዳደራል የሁሉ ፈጣሪ ነው ኃይሉ እጅግ ታላቅ ነው ጐበዝ ነን ያሉ ይወድቃሉ ኃይለኞች ደግሞ ይደክማሉ ጌታን መመኪያ ያደረጉ ሕይወታቸውን ለርሱ የሰጡ ይወጣሉ ይሮጣሉ ከቶ አይደክሙም ያሸንፋሉ ከፍታውን ይይዛሉ እወጣለሁ ገና እሮጣለሁ ከቶ አልደክምም አሸንፋለሁ ከፍታውን እይዛለሁ እይታዬ እግዚአብሔር ነው የእኔስ ኑሮ ሰማያዊ ነው አምኖ በምድር አሰማርቶኛል ማንነቴን ተርክ ብሎኛል ለተጠማ እርካታ ለደከመው ጉልበት ላዘነው ደስታ ይህን እንደሚሰጥ ነው ማውቀው የእኔ ጌታ (2x) ይሄ ነው የተጻፈው ይሄ ነው ለእኔ የተባለልኝ (4x)