ኧረ ምን ይባል ምን ይባል ይህ ጌታ እኔ ምለው አጣሁ አስገረመኝ ጌታ ምነው ሌላ ነገር ሌላ ነገር ባይኖር ቀንና ሌሊቱን እልል ሲባል ሲመለክ ቢታደር በህልውናው ውስጥ እልም ጥፍት ስምጥ ብሎ ማደር አዝ፦ እንደ ባለሃምሳ ቀን እንደ መጀመሪያው ና ደግመህ በሕይወቴ ና ደግመህ በሕይወቴ ሙላኝ በመንፈስህ ልሂድ ወደሰማይ ልሂድ ወደሰማይ (2x) ከአቻምናው የአምናው የዘንድሮው ባሰ በተጠጋሁት ቁጥር ሕይወቴ እየራሰ እየረሰረሰ ህልውናውን ወደድኩ ከሁሉ የበለጠ መገኘቱን ናፈቅሁ ከሁሉ የበለጠ ኢየሱሴን ወደድኩ ከሁሉ የበለጠ ኢየሱሴን ናፈቅሁ ከሁሉ የበለጠ አዝ፦ እንደ ባለሃምሳ ቀን እንደ መጀመሪያው ና ደግመህ በሕይወቴ ና ደግመህ በሕይወቴ ሙላኝ በመንፈስህ ልሂድ ወደሰማይ ልሂድ ወደሰማይ (2x) ሁልጊዜ አዲስ ነገር አዲስ ነገር አለህ ቢቀዳ ቢቀዳ እንደማያልቅ እንደመልካም ምንጭ ነህ ምን ብዬ ልግለጽህ (የእኔ ጌታ) ምን ብዬ ልናገር እጅጉን ድንቅ ነህ (2x) ዋላ የውኃ ምንጭ ሁሌ እንደምትናፍቅ (2x) ነፍሴ አንተን ተጠማች አንተን ፈለገችህ (2x) ማለዳ ተነስታ ኢየሱስ ኢየሱስ (2x) ኢየሱስ አለችህ ዋላ የውኃ ምንጭ ሁሌ እንደምትናፍቅ (2x) ነፍሴ አንተን ተጠማች አንተን ፈለገችህ (2x) ማለዳ ተነስታ ኢየሱስ ኢየሱስ (2x) ኢየሱስ አለችህ