አዝ፦ በማለዳ ምሥጋናዬ በሌሊትም ዝማሬዬ ይዤ ልቅረብ ወደ ፊትህ ቤትህን ይሙላው ያውድልህ (2x) ሰዎች ሰውን አይተው ያፈገፍጋሉ የሕይወትን መንገድ ጥለው ይሄዳሉ እኔ ግን ባሰብኝ ጨመረብኝ ፍቅሩ አልሻም ለሰከንድ መውጣት ከድንበሩ አልሻም ለሰከንድ መውጣት ከድንበሩ እልሻም ለሰከንድ መውጣት ከክልሉ (2x) አዝ፦ በማለዳ ምሥጋናዬ በሌሊትም ዝማሬዬ ይዤ ልቅረብ ወደ ፊትህ ቤትህን ይሙላው ያውድልህ (2x) በምድር እስካለሁ እኔ እናገራለሁ ብዙ ተደርጐልኝ ብዙ አይቻለሁ የማይገባኝን ሆኖልኝ እያየሁ ክብር ለሚገባው ክብር ይሁን እላለሁ ጐንበስ ቀና ብዬ አመልከዋለሁ (4x) እኔስ (4x) እኔስ እንደገና ቃልን እገባለሁ ሃሳብህን ይዤ ሃሳቤን እጥላለሁ የወደድከው ይሁን አባ እኔ እኔ እታዘዛለሁ አንተን ደስ ካለህ ሌላ ሌላ ምን እፈልጋለሁ (2x)