አዝ፦ ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው ያው ነው ጌታዬ ያው ነው ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው ያው ነው አምላኬ ያው ነው ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (2x) (ሃሌሉያ) ባህሩን በተዓምር የከፈለ አንካሳውን ደግሞ ያዘለለ እውሩን በእጆቹ ዳሰሰና በሰላም ሂድ አለው ፈወሰና (2x) ጴጥሮስን በውሃ ላይ ያራመደ ማዕበል ወጀቡን ጸጥ ያረገ እንደሱ የሚሆን የትም የለም ይባረክ ይመስገን ለዘላለም (2x) አዝ፦ ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው ያው ነው ጌታዬ ያው ነው ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው ያው ነው አምላኬ ያው ነው ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (2x) (ሃሌሉያ) ምንም በሌለበት ምድረ በዳ ሕዝቡን የሚመግብ የሚረዳ በጠሩትም ጊዜ ከተፍ የሚል የሚያኮራ ጌታ የሚያስተማምን በጠሩትም ጊዜ ከተፍ የሚል የሚያኮራ ጌታ የሚያስተማምን (2x) ዛሬም ለኔ (ዛሬም ለኔ) በዘመኔ (በዘመኔ) ድንቅ አድርጐልኛል ኢየሱስ ጌታዬ (2x) አዝ፦ ያው ነው እግዚአብሔር ያው ነው ያው ነው ጌታዬ ያው ነው ያው ነው ኢየሱስ ያው ነው ያው ነው አምላኬ ያው ነው ጥንትም የሚሰራ አሁንም ያው ነው አልተለወጠም ኃይሉ ሙሉ ነው (2x) (ሃሌሉያ) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል ጥራኝ እኔ ደግሞ እሰማሃለሁ የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገር አሳይሃለሁ በቃሌ እኔ እተጋለሁ ድምጽህን ፈጥኜ እሰማለሁ ከቃሌ ጋራ እሆናለሁ ብቻ አንተ እመን እሰራለሁ (2x) ዛሬም ለኔ (ዛሬም ለኔ) በዘመኔ (በዘመኔ) ድንቅ አድርጐልኛል ኢየሱሱ ጌታዬ (2x)