አዝ:- ተመስገን ተመስገን ጌታችን ተመስገን በእውነት ተመስገን ከልባችን ተመስገን (2x) ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ ቀን በደመና አምድ ሌሊት በእሳት አምድ ዛሬም በዚህ አለ ሊመራ ሊያሳድግ እባክህ አትሂድ በራስህ መንገድ (3x) አዝ:- ተመስገን ተመስገን ጌታችን ተመስገን በእውነት ተመስገን ከልባችን ተመስገን (2x) ዳንኤል በእግዚአብሔር ፊት መስኮት በሩን ከፍቶ ይጸልይ ጀመረ ለአምላክ ተንበርክኮ ጠላትም ሊያጠፋው ምክርን ሁሉ መክሮ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው በቃ አለቀ ብሎ ከእሱ ጋራ ያለው ከሁሉም ይበልጣል በአንበሳ መካከል እንቅልፍን ይሰጣል አንተን የሚያስፈራህ ዛሬ የትኛው ነው እባክህ በርሱ ታመን እርሱ ሁሉን ቻይ ነው (3x) ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ አመታቶችን አሳልፎ ቀኖቹን በመልካም ለውጦ እዚህ ደረስኩኝ በጌታ ምህረቱ በዝቶ እዚህ ደረስኩኝ በኢየሱስ ምህረቱ በዝቶ (2x) ጠላት ያሰበው በኔ ላይ አልሆነም እቅዱም ከቶ አልተከናወነም እግዚአብሔርን ለሚወዱ እንደ ሃሳቡም ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ለመልካም እንደሚደረግ እኔ አወቅኩ እንደሚደረግ ተረዳሁ (2x) እስኪ ያለፈ ሰው የታል የተሸጋረ አሮጌው ልብሱ በአዲስ የተቀየረ ጭጋግ ጨለማው እንደጉም የተበተነ ሆ ይበል በምስጋና ይግባ ወደ መቅደሱ ለጌቶች ጌታ ይዘምር ያምጣ/ያግባ ስለቱን (2x) ዝም ብዬ እዘምራለሁ ለኔ የሚያስብ ጌታ አግኝቻለሁ (2x) ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ ሹመት ከፍታን ከፊቴ እያየሁ ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ በተራራ ላይ እቀመጣለሁ ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ ትልቅነቱን እናገራለሁ አንድ ጌታ አንድ አምላክ አንድ ወዳጅ አለ ለዓለም ቤዛ መድህን መልስም የሆነ (2x) እርሱ ነው ቤቴን የለወጠው ታሪኬን ከስር የገለበጠው (2x) በአዲሱ አቅማዳ አዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈሳል ከኔ ወደ ደጅ ያረካል እርሱ እኔ ረክቻለሁ ግቡና ጠጡ ጋብዣችኋለሁ (2x) ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) ኢየሱስ መልስ ነው (2x) ወግ ማዕረግ በርሱ ነው (7x) ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ አመታቶችን አሳልፎ ቀኖቹን በመልካም ለውጦ እዚህ ደረስኩኝ በጌታ ምህረቱ በዝቶ እዚህ ደረስኩኝ በኢየሱስ ምህረቱ በዝቶ ጠላት ያሰበው በኔ ላይ አልሆነም እቅዱም ከቶ አልተከናወነም እግዚአብሔርን ለሚወዱ እንደ ሃሳቡም ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ ለመልካም እንደሚደረግ እኔ አወቅኩ እንደሚደረግ ተረዳሁ (2x) እስኪ ያለፈ ሰው የታል የተሸጋረ አሮጌው ልብሱ በአዲስ የተቀየረ ጭጋግ ጨለማው እንደጉም የተበተነ ሆ ይበል በምስጋና ይግባ ወደ መቅደሱ ለጌቶች ጌታ ይዘምር ያግባስለቱን (2x) ዝም ብዬ እዘምራለሁ ለኔ የሚያስብ ጌታ አግኝቻለሁ (2x) ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ ሹመት ከፍታን ከፊቴ እያየሁ ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ በተራራ ላይ እቀመጣለሁ ነገንም በርሱ እረማመዳለሁ ትልቅነቱን እናገራለሁ አንድ ጌታ አንድ አምላክ አንድ ወዳጅ አለ ለዓለም ቤዛ መድህን መልስም የሆነ (2x) እርሱ ነው ቤቴን የለወጠው ታሪኬን ከስር የገለበጠው (2x) በአዲሱ አቅማዳ አዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈሳል ከኔ ወደ ደጅ ያረካል እርሱ እኔ ረክቻለሁ ግቡና ጠጡ ጋብዣችኋለሁ (2x) ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) ኢየሱስ መልስ ነው (2x) ወግ ማዕረግ በርሱ ነው (7x)